በጣም ገራሚ ነገር የጃልመሮ የስልክ ንግግር ወጣ

ጋዜጠኛ፡ በምዕራብ ወለጋ ስልክ የለም እንደተቋረጠ ይታወቃል፤ ያንተ ስልክ ግን ይሄው ይሰራል እያወራን ነው፤ ይሄ ነገር እንዴት ነው? አይጋጭም? አሁን ስታወራኝ ኔትወርክ አለ፤ ከየት አመጣኸው ኔትወርኩን?

ጃልመሮ፡ ጋዜጠኛ ብዙ አታናግረኝ፤ አንተ… … ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቦታ ሆኔ ስራዬን ማከናወን ነው የሚጠበቅብኝ የትም ይሁን የት፡፤ አንተ ስልኬን አግኝተህ እንደደወልክልኝ ፍንፍኔ ሆኘ ስራየን ማከናወን እችላአለሁ፤ የሚከለክለኝ ሰው የለም…

ሙሉ ቃለምልልሱን ከስር ማዳመጥ ትችላላችሁ፡፡ እኔ ግን የራሴን አስተያየት ትንሽ ላክልበት፡፡ ምዕራብ ወለጋ ስልክና ኢንተርኔት መዘጋቱ የሚታወቅ ነው (ይሄንን ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ፓርላማ ላይ በይፋ ተናግረዉታል)፡፡ የሚገርመው ግን የጃልመሮ ስልክ መስራቱ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሁለት መላ ምቶችን መገመት ይቻላል፡፡ አንደኛው ጃልመሮ እዚያው ወለጋ ስልክ ከተዘጋበት ቦታ ከጦሩ ጋር ሆኖ በልዩ የሱን ስልክ ብቻ እንዲሰራለት ተደርጎ (ይህ በቴክኖሎጅው የሚቻል ስለሆነ)፤ ሁለተኛው ሌላ ቦታ ምናልባትም እሱ እንዳለው ፍንፍኔ (አዲስ አበባ) ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ በሁለቱም ኬዝ የመንግስት እጅ አለበት ማለት ነው፡፡ ታዲያ መንግስት ሆን ብሎ ለኦነግ ድጋፍ እያደረገ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዉስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ልጆች ለምን ያስጨርሳል?

በቃለምልልሱ ላይ ጃልመሮ እንዳለው በመከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ተናግሯል፤ እንዲያዉም ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚባል የለም ዉሸት ነው ብሏል፡፡ እኛ ነን ጀግኖቹ ማለቱ ነው፡፡ እንዴት ከ50 ዓመት በላይ ታግሎ አንድም ድል ማግኘት ያልቻለው ኦነግ ዛሬ በድንገት እንዴት ይሄን ሁሉ ጀግንነት አገኘ? 50 ዓመት ሙሉ በትግል ላይ ሲቆይ እንዳያሸንፍ ብሎም ጭራሹን ስሙ እንኳን ሀገር ዉስጥ እንዲጠፋ ያደረገው ጀግናው መከላከያ ሰራዊት ዛሬ እንዴት በኦነግ ሊጠቃ ቻለ? እዉነት መንግስት ከኦነግ ጋር ወይስ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ነው? ሙሉ ቃለምልልሱን አድምጡትና አስተያየታችሁን ከስር ብትሰጡበት እላለሁ፡፡

Share this article:
Previous Post: በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ ለተፈጠሩ ችግሮች ተጠያቂው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ነው

February 9, 2020 - In Articles

Next Post: Project Manager – Job Vacancy in Ethiopia

February 9, 2020 - In Uncategorized

Related Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published.