ድንቃድንቅ ወሬዎች : ሞትን ድል ያደረገችው ህጻን

በህይወት ውስጥ ለሚከሰቱ አንዳንድ ጉዳዮች በሳይንሳም ሆነ በህክምናው ዘርፍ ማብራሪያ ለመሰጠት በጣም አዳጋች ሆነው ይገኛሉ፡፡ የዚህ አይነቱ ክስተቶች ተዓምራዊ የሚል ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡

የ 27 አመቷ አውስተራሊያዊት ኬት ኦግ የመንትያ ህጻናት ፅንስ እንዳላት በህክምና ባለሙያዎች ከተነገራት ቆይታለች፡፡ መንትያዎቹ ህጻናት፤ ጄሚና ኤሚ በእናታቸው ማህጻን ውስጥ መቆየት የቻሉት ግን ለ27 ሳምንታት ብቻ ነበር፡፡

መንትያዎቹ  በ 7 ወር ገደማ ከተወለዱ በኃላ ከመንትዮቹ አንዷ የሆነችው ኤሚ ባጋጠማት አስቸጋሪ የጤንነት ሁኔታ የህክምና ባለሙያዎቹ የተቻላቸውን ድጋፍ ቢያደርጉም፤ ህጻኗን ኤሚ ህይወት መታደግ እንዳልቻሉ ለህጻናቱ እናት ኦግ አረዷት፡፡ እንድትሰናበታትም አስታቀፏት፡፡

የእናት ነገር ሆኖ እንኳን የሞተ ልጃቸውን ይቅርና ጤነኛ ልጃቸውን ለመሰናበት የሚያስችል አንጀት ስላሌላቸው፤ እናት ኦግ ኤምሊን በሀኪሞች ህይወቷ አልፏል የተባለችውን ህጻን ለሁለት ሰዓታት ያክል በደረቷ ላይ( በጡቶቿ) መሃከል አቅፋት ቆየች፡፡

ምንጭ: የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
Posted by ashu on 06/04/2015 07:35 PM