ድንቃድንቅ ወሬዎች

ድንቃድንቅ እና አስገራሚ ጨዋታዎችንና መጣጥፎችን እዚህ ያገኛሉ

የሳይኮሎጂዉ ፕሮፌሰር

የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩ ወደ ክፍል ገብቶ የእለቱን ወሳኝ ትምርት ለመጀመር ወደ ቦርድ እንደዞረ ፉጨት ሰማ።
ወደ ተማሪዎቹ ዞሮ ማን እንዳፏጨ ጠየቀቃቸው ፣ሁሉም ዝም አሉ።

ፕሮፊሰሩ ተረጋግቶ ፣እስክሪቢቶውን ወደ ኪሱ እየከተተ ፣የዛሬው ሌክቸር እዚ ላይ ያበቃል፣ፈገግ ብሎ ነገር ግን መጀመሪያ አንድ ታሪክ እነግራችዋለው አላቸው።ሁሉም በጉጉት መጠበቅ ጀመረ

" ትላንት ቤቴ እንቅልፍ ስላስቸገረኝ ፣ዝም ብዬ ተነስቼ ነዳጅ ልሞላም በዛውም ልናፈስ ለዛሬም ጊዜ ለመቆጠብ ከመሽ ወጣሁ🚗🚗🚗,ነዳጅ ከሞላሁ በኋላ ከትራፌክ ነጻ የሆነው መንገድ ላይ እየተንሸራሸርኩ ከሆነ ፖርቲ ነገር የወጣች የምትመል ቆንጂዬ ወጣት አየሁ።

መኪናዬን አዙሬ እርዳታ እንደምትፈልግ ጠየኳት "ታክሲ እንዳጣች እና ቤቷ እንዳደርሳት ነገረችኝ"

ጋቢና ገባች....ማውራት ጀመርን....ውበት ብቻ ሳይሆን ባወራነው ርእስ ሁሉ  በጣም ስማርት ጭንቅላት እንዳላት ከምታወራው መገመት ቻልኩ።

ቤቷ እንደደረስን ፣በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ነገረችኝ፣እኔም ጥሩ አስተሳሰብ እንዳላት ነግሬአት እንደወደድኳት ነገርኳት፣ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር እንደሆንኩ አውርተን ፣ስልክ ተለዋወጥን።
አንድ ነገር ላስቸግርህ ስትለኝ ፣ምንም ችግር የለውም አልኳት ።"ወንድሜ አንተ የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነው፣በኛ ግንኙነት እንዳይጎዳ ቃል ግባልኝ" አለችኝ ....ችግር የለም ብዬ ስሙን ጠየኳት።አንድ መለያ ባህሪ አለው በሱ ታውቀዋለህ፣ፉጨት ማፏጨት ያዘወትራል። አለችኝ

ከዛ ሁሉም ተማሪ ወደ አፏጨው ልጅ ዞሮ ማየት ጀመረ

ፕሮፌሰሩ
"የሳይኮሎጂ PHD ዬን አልገዛውትም፣ሰርቼ ነው ያገኘውት ና ውጣ "🙆‍♂😂😂
Posted by ashu on 20/09/2019 06:20 PM
0 comments
 

Archives